ሸዋል ኢድ በዓል

ሸዋል ኢድ በዓል

የሀረሪ ክልል ብቸኛው ክልላዊ በዓል የሆነው የሸዋል ኢድ በዓል የኮሮናቫይረስ ባሳደረው ተፅዕኖ በአደባባይ ባይከበርም በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት በዓሉ ሁሉም በየቤቱ እንዲያከብረው መደረጉን የሀረሪ ክልል አስታወቀ።

ከ15ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ በሀረር መከበር እንደተጀመረ የሚገመተው ሸዋል ኢድ ከሀይማኖታዊነቱ ይልቅ ባህላዊነቱ የጎላ ነው ይባላል።

ከድሬዳዋ፣ አዲሰ አበባና ከውጭ ሃገራት ጭምር ሀረሪዎች በሀረር ከተማ ተሰብስበው የሚያከብሩት የሸዋል ኢድ በዓል የሀረሪዎች ዋነኛ የመተጫጫ ቀን ነውም ይባላል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ሸዋል ኢድ በዓል