በታመሰው የበርማ ራኺኔ ክፍለ ግዛት ሰባት ሰዎች በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ተመተው መገደላቸው ተዘገበ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ትናንት ማክሰኞ ማታ ምራኡክ ዩ በምትባለው ከተማ ከአንድ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል ተከትሎ አራት ሺህ የሚሆኑ ሰዎች አንድ የመንግሥት ህንፃ መውረራቸውን የገለፁት የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ከዚያም ፖሊሶች ህዝቡን ለመበተን ወደሰማይ የጎማ ጥይት ተኩሰዋል፡፡ ነገር ግን ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች ላይ ጣቃት ማድረስ ሲጀምሩ ፖሊሶች መተኮስ ጀመሩ ብለዋል ።
ከተገደሉት ሌላ አስራ ሦስት ሰዎች በጥይት መቁሰላቸው ታውቋል። የተገደሉትና የቆሰሉት ሰዎች ቡዳሃ ዕምነት ተከታዮች እንጂ ሮሂንጃዎች እንዳልሆኑ ነው የተዘገበው። አምነስቲ ኢንተርናሽናል በነፃ አካል እንዲመረመር አሳስቧል።