ወደ ዋግኽምራ የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ዞኑ አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

ወደ ዋግኽምራ የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ዞኑ አስታወቀ

በህወሓት ቁጥጥር ሥር ናቸው ከተባሉ አካባቢዎች ተፈናቅለው ወደ ዋግኽምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የዞኑ ኮሚኒኬሽን መምሪያ ገለፀ።

በከተማው በአሁኑ ሰዓት ከ70 ሺ በላይ ተፈናቃይ እንዳለ የገለፁት መምሪያ ኃላፊው አቶ ከፍያለው ደበሽ በየቀኑ ቁጥሩ እስከ 200 የሚደርሱ ተፈናቃዮች ወደ ከተማው እየገቡ መሆኑን ተናግረዋል።

ተፈናቃዮቹ በአካባቢው የሚበላ ነገር አለመኖሩንም ለመፈናቀላቸው ምክኒያት እንደሆናቸው ተናግረዋል።