“ይሄ ፊልም ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፏል። ብዙ ላብ ፈሶበታል። ... ልክ እንደ ሥሙ መቋጫ የሌለው ዙር ሆኖ ይነጋል ይመሻል። ቀረጻ ይቀረጻል። ... ዙሩ አላልቅ ስላለ ብዙዎች እንደ ምትሃት አይተውት ነበር።” ተመስገን አፈወርቅ የተከታታይ ፊልሙ ደራሲ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
Your browser doesn’t support HTML5
ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ምሽት የተዋወቀ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ነው፤ የተከታዩ ቅንብር ትኩረት።
ታዋቂና አዳዲስ ተዋናዮች የተሳተፉበትና .. ቀጣይ ነውና ወደፊትም የሚሳተፉበት፤ የሁለት ዓለም ሕይወት ሊያስተሳስር የታለመ ትዕይንት ነው።
ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ በምትገኘው የሲልቨርስፕሪንግ ከተማ ድራማው የተዋወቀበትን ሥነ ሥርዓት ተከታትለናል።
አዎን የሁለት ዓለም ጫፎች ሕይወት ... ዋሽንግተንና አዲስ አበባን በቴሌቭዥን መስኮት ሊያነካካ፥ ሊያስተሳስር፤ የስደትን ሕይወት ቀለሞች ሊያሳይ እና (ባለታሪኮቹ) ከትውልድ ሃገራቸው ጋር ያላቸውን የጠበቀና አንዳንዴም ወልፈት የማያሳኝ የሚመስል ትስስር ሊፈነጥቅ፤ ይልቁንም የሚኖሩበትን አገር ፈተናዎችና የኑሮ ቃና ሊያሳይ በአሜሪካ የሚሠራና ከአሜሪካ የሚሰራጭ ተከታታይ ፊልም ነው።
በዩናይትድ ስቴትስ ተሰርቶ ወደ ኢትዮጵያ ሲሰራጭ የመጀመሪያው እንደሚሆን የተነገረለት የተከታታይ ፊልም ሥራ የራሱን ታሪክ የጻፈም ይመስላል።
የሙዚቃ አቀናባሪዎችና ሌሎች አጋዥ ባለሞያዎች ጨምሮ ከሰላሳ በላይ ሰዎች የተሳተፉበት ተከታታይ ድራማ የፊታችን ቅዳሜ በEBS ቴሌቭዥን ምሽት መታየት ይጀምራል።