በሴኔጋል ሁከት 16 ሞቱ፤ ከ500 በላይ ተጎዱ

  • ቪኦኤ ዜና

በሁከቱ የወደሙ ሱቆች ዳካር፣ ሴኔጋል

በሴኔጋል፣ በተቃዋሚው መሪ ኦስማን ሶንኮ ላይ፣ በአንድ ፍርድ ቤት የሁለት ዓመት ቅጣት መተላለፉን ተከትሎ በተነሳ የደጋፊዎቻቸው ተቃውሞ፣ 16 ሰዎች ሲሞቱ 350 የሚኾኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ፖሊስ የወሰደውንና “ጨካኝ” ያሉትን ርምጃ እንደሚያወግዙ ሶንኮ አስታውቀዋል። የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ 500 የሚደርሱ ሰዎች፣ በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ አስታውቀዋል።

ባለፈው ኀሙስ በጀመረው ሁከት፣ አንድ ነፍሰ ጡር እና 36 የጸጥታ አባላትን ጨምሮ 357 ሰዎች እንደተጎዱ፣ ቀይ መስቀል አስታውቋል። ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባሉ 78 ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

ፕሬዚዳንት ማኪሳልእና የሶንኮ ደጋፊዎች፣ አንዳቸው ሌላቸውን ለሁከቱ ተጠያቂ ያደርጋሉ። ሶንኮ፣ በመጀመሪያ የተከሠሡ በአስገድዶ ነበር፡፡ ቆይቶ ግን “አንዲት ወጣት ሴትን ከሥነ ምግባር ያፈነገጠ ተግባር እንድትፈጽም በማድረግ” ወደ ሚል ክሥ ተቀይሯል።

ክሡ ፖለቲካዊ እና እርሳቸው በሚቀጥለው ዓመት በምርጫ እንዳይወዳደሩ ለማድረግ የተወጠነ እንደኾነ፣ ሶንኮ ይገልጻሉ።