ነፍሰ ጡሯን የፓርላማ አባል የደበደቡ የሴኔጋል ፓርላማ አባላት ታሰሩ

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል፦ የሴኔጋል ፓርላማ

ፎቶ ፋይል፦ የሴኔጋል ፓርላማ

ሴኔጋል ፓርላማ ውስጥ በተፈጠረ ረብሻ ነፍሰ ጡር በሆኑ የገዢው ፓርቲ ተወካይ ላይ ድብደባ ያደረሱ ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ታስረዋል።

የሴኔጋል ፍርድ ቤት ሁለቱን የፓርላማ አባላት በስድስት ወር እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ሰጥቷል።

በታህሳስ መጀመሪያ በተካሄደው የፓርላማው ጉባኤ ላይ በቴሌቭዥን በታየው ሁከት የተቃዋሚ ፓርቲ አባሉ ማሳታ ሳምብ የገዢው ቤኖ ቦክ ያካር ተወካዮን ኤሚ እንዳዬን በጥፊ ሲመቷቸው እና እሳቸውም በወንበር አንሰተው ወርውረውባቸዋል።

ከዚያም ሌሎች የምክር ቤት አባላት ገፍተረው ከጣሏቸው በኋላ ሆዳቸው ላይ በዕርግጫ መትተዋቸዋል። ጥቃቱን ያደረሱባቸው ሁለቱ የምክር ቤቱ አባላት የ8200 ዶላር ካሳ እንዲከፍሏቸው ዳኛው አዝዘዋል።