ድምፃዊት ሴና ሰለሞንና ሰባት ተከሳሾች የማረሚያ ቤቱን አያያዝ አማረሩ

ኦሮመኛ ድምፃዊት ሴና ሰለሞንን ጨምሮ ሰባት የኪነጥበብ ባለሞያዎች በማረሚያ ቤት ያለውን አያያዛቸው ሰብዓዊ መብትን የጣሰ መሆኑን በመግለጽ አማረሩ። "ከዚህ ማረሚያ ቤት ተርፈን የምንወጣ አይመስለንም” ብለዋል።

ከተከሳሾቹ ጠበቃ አንዱ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ያለው አያያዛቸው ሰብዓዊ መብታቸውን የጣሰ መሆኑን አስረድተዋል ብለዋል።

አቤቱታቸውን ካቀረቡት መካከል በተለይ አራተኛው ተከሳሽ ኢፋ ገመቹ ፤ “የእርሶ ልጅ (ዳኛውን ማለቱ ነው) ነገ መብቱን ከጠየቀ መታሰሩ አይቀርም። ስለዚህ ስለ እርሶም ልጅ ብዬ ነው የምናገረው። የምንጠቀመው ውሃ የጉድጓድ ውሃ ነው! አሸዋ ነው ያለው። ትል ነው ያለው። ሙቅ ነው በዛ ላይ። እዚህ የምታዩት ጠቅላላ ኩላሊት በሽተኛ ነው።” ሲል በምሬት ተናግሯል ተብሏል።

ጽዮን ግርማ ጠበቃ አቶ ወንድሙ ኢብሳን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

Your browser doesn’t support HTML5

ድምፃዊት ሴና ሰለሞንና ሰባት ተከሳሾች የማረሚያ ቤቱን አያያዝ አማረሩ