አቶ የሺዋስ አሰፋ"አስፈሪ ማስጠንቀቂያ" ተሰጥቷቸው ከእስር መለቀቃቸውን ተናገሩ

  • መለስካቸው አምሃ

አቶ የሺዋስ አሰፋ

በሰማያዊ ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን አመራር አባላት ላይ ዓቃቤ ሕግ የመሰረተውን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ የክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

በሰማያዊ ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን አመራር አባላት ላይ ዓቃቤ ሕግ የመሰረተውን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ የክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ትናንት በባህር ዳር ከተማ የፀጥታ ኃይል አባላት ነን ባሉ ሰዎች ለሰዓታት ተይዘው ከቆዩ በኋላ ተለቀቁ፡፡ አስፈሪ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውም፣ ተናገሩ፡፡

የአማራ ክልል ዓቃቤ ሕግ ዘጠኝ በሚሆኑ የምዕራብ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላትና ሌሎች አባላት ላይ የተመሰረተውን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ዛሬ የክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደሰጠ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ለቪኦኤ ገለፁ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

አቶ የሺዋስ አሰፋ"አስፈሪ ማስጠንቀቂያ" ተሰጥቷቸው ከእስር መለቀቃቸውን ተናገሩ