የኮረም እና ኦፍላ አካባቢዎች ተፈናቃዮች አስቸኳይ የድጋፍ ጥያቄ እያቀረቡ ናቸው

Your browser doesn’t support HTML5

የኮረም እና ኦፍላ አካባቢዎች ተፈናቃዮች አስቸኳይ የድጋፍ ጥያቄ እያቀረቡ ናቸው

ከኮረም እና ኦፍላ ወረዳዎች ተፈናቅለው ወደ ሰሜን ወሎ እና ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ዞኖች ተጠልለዋል የተባሉ ከ35ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች፣ ከወር በላይ ያለምንም የምግብ ድጋፍ መቀመጣቸውን ገለጹ።

የኮረም ከተማ አስተዳደር፣ በተፈናቃዮቹ ላይ ደርሷል ስላለው ሰብአዊ ጉዳት ለሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሽ አለማግኘቱን ገልጿል፡፡ የፌደራል አካላት እና የክልሉ መንግሥትም “ለችግሩ በቂ ትኩረት አልሰጡም፤” ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። በጉዳዩ ላይ፣ ከክልሎቹ እና ከፌደራሉ መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።