በጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ማብራሪያ ላይ የባለሙያዎች ምልከታ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ

ኢትዮጵያ ተጨማሪ ብድሮችን ለማግኘት ለአምስት አመታት ከአበዳሪ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር እያደረገቻቸው ያሉ ድርድሮች በአብዛኛው ተቀባይነት እያገኙ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልጸዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራርያ ላይ እንዳሉት ይህም ከተሳካ ተጨማሪ 10.5 ቢሊዮን ዶላር ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመታት እንደምታገኝ ተናግረዋል::

Your browser doesn’t support HTML5

በጠቅላይ ሚንስትሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ማብራሪያ ላይ የባለሙያዎች ምልከታ

በውጭ ምንዛሬ እጥረት እየተፈተነች ባለቸው ኢትዮጵያ ተጨማሪ ብድር መገኘቱ ኢኮኖሚውን ሊያነቃቃው እንደሚችል የሚናገሩት የአሜሪካ ድምጽ ያናገራቸው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ነገር ግን ይህም ተጨማሪ እዳ ለሃገሪቱ እንዳያስከትል ከወዲሁ ትክክለኛ የልማት ስራዎች መለየት ያስፈልጋል ይላሉ::

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡