የሳውዲ አረብያ ንጉሥ የባለሥልጣናት ብወዛ አካሂደው ወታደራዊ መኮንኖችና ሚኒስትሮች ቀያይረዋል

  • ቪኦኤ ዜና
የሳውዲ አረብያ ንጉሥ ሳልማን በመከላከያ ተቋሙ ውስጥ ስፋት ያለው የባለሥልጣናት ብወዛ አካሂደው አንዳንዶቹን ዋና ዋና ወታደራዊ መኮንኖችና ሚኒስትሮች ቀያይረዋል።

የሳውዲ አረብያ ንጉሥ ሳልማን በመከላከያ ተቋሙ ውስጥ ስፋት ያለው የባለሥልጣናት ብወዛ አካሂደው አንዳንዶቹን ዋና ዋና ወታደራዊ መኮንኖችና ሚኒስትሮች ቀያይረዋል።
አዳዲስ የአየር መከላከያ የምድር ጦር አዛዦች የሾሙ ሲሆን በሀገር ግዛት ሚኒስተሩ ውስጥም የከፍተኛ ሹማማንት ለውጥ ማካሄዳቸውን በመንግሥቱ የዜና አውታር በተነበበው ዐዋጅ ተነግሯል።
የባለሥልጣናት ብወዛው በምን ምክንያት እንደሆነ አልተገለፀም። ሌተና ጀነራል ፋያድቢን ሃሜድ አል ሩዋይሊ አዲሱ የቤተ መንግሥቱ ጽሕፈት ቤት ሹም ሆነው ተሾመዋል።