የመን ሆዴይዳ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል

በስደት ያለውን የየመን መንግሥት የሚደግፈው በሳውዲ አረብያ የሚመራው ጥምረት ሆዴይዳ በተባለችው ዋና የወደብ ከተማ ላይ ዛሬ ወረራ ከፍቷል።

በስደት ያለውን የየመን መንግሥት የሚደግፈው በሳውዲ አረብያ የሚመራው ጥምረት ሆዴይዳ በተባለችው ዋና የወደብ ከተማ ላይ ዛሬ ወረራ ከፍቷል።

ሑቲ አማፅያን ሆዴይዳንና የየመን መዲና ሰንዓን ይቆጣጠራሉ። የጥምረቱ አካል የሆነው የተባበረው የአረብ ኤምሬቶች ሁቲዎች ከወደብ ከተማይቱ እንዲወጡ የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ዛሬ ማለፉን ገልጿል።

ሐደይዳ ወደብ ምግብና ረድዔት ወደ ሀገሪቱ ለማስገባት ወሳኝ ከተማ ናት። በሁቱዎችና በአቡ ራቡ ማንሱር ሃዲ መንግሥት መካከል ከሦስት ዓመታት በፊት ግጭት ከመጀመሩ በፊትም ቢሆን ሀገሪቱ በምግብ ዋስትና ዕጦት ስተሰቃይ ቆይታለች። በአሁኑ ወቅት ከ20 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች የምግብ ረድዔት እንደሚያስፈልጋቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጿል።