ዩናይትድ ስቴትስ ለሶሪያ እና ኢራቅ የ150 ሚ. ዶላር ርዳታ እንደምትሰጥ አሰታወቀች

  • ቪኦኤ ዜና

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ አገራቸው ዩናይትድ ስቴትስ፣ በሶሪያ እና በኢራቅ፥ ከእስላማዊ መንግሥት አክራሪ ቡድኑ (ISIS) ነፃ ለወጡ አካባቢዎች የሚውል፣ የ150 ሚሊዮን ዶላር ርዳታ እንድምትሰጥ፣ ዛሬ ኀሙስ አስታወቁ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ አገራቸው ዩናይትድ ስቴትስ፣ በሶሪያ እና በኢራቅ፥ ከእስላማዊ መንግሥት አክራሪ ቡድኑ (ISIS) ነፃ ለወጡ አካባቢዎች የሚውል፣ የ150 ሚሊዮን ዶላር ርዳታ እንድምትሰጥ፣ ዛሬ ኀሙስ አስታወቁ፡፡

ብሊንከን ይህን ያስታወቁት፣ የእስላማዊ መንግሥት ቡድኑን ለመዋጋት፣ በሚኒስትሮች ደረጃ፣ በሳዑዲ አረብያ በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት፣ ቡድኑ የተቆጠጣረው አንዳችም ግዛት ባይኖርም፣ ተባባሪዎቹ ግን አሁን ድረስ፣ በአፍሪካ፣ በእስያ እና በመካከለኛው ምሥራቅ ጥቃት እየሰዘነሩ እንደኾነ ተነግሯል፡፡

አይሲሲን ለማሸነፍ የተቋቋመው ዓለም አቀፍ ጥምረት፣ ከ80 በላይ አገሮችን ያካተተ ሲኾን፣ ከፍተኛውን የሶሪያ እና የኢራቅ አካባቢዎችን በተቆጣጠረው ጽንፈኛው ቡድን ላይ የተቀናጀ ርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ፣ አሶሽዬትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንዳመለከቱት፣ የአሁኑ የዩናይትድ ስቴትስ የ150 ሚሊዮን ዶላር ርዳታ፣ በቀጣይ፣ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያድገው የዐዲሱ የገንዘብ ድጋፍ አካል ነው፡፡

ብሊንከን፣ “የተዳከሙ የደኅንነት እና የሰብአዊነት ኹኔታዎች፣ የምጣኔ ሀብት ዕድል ዕጦት የመሳሰሉት፣ አይሲስ የሚያቀጣጥላቸውና ተከታዮችን ለመመልመል የሚጠቀምባቸው አሳዛኝ ኹኔታዎች ናቸው፤” ሲሉ፣ በአክራሪው ቡድን የተለመዱትን አባባሎች ተጨባጭ መፍትሔ እንደሚያሻቸው ገልጸዋል፡፡

ብሊንከን፣ በሳዑዲ አረቢያ ከሚያደርጉት የሁለት ቀናት ጉብኝት ጋራ በተያያዘ፣ አብረው በአዘጋጁት በዚኹ ስብሰባ አጋጣሚ፣ ከልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማንና ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋራ ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡ በባሕረ ሠላጤው ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባም ላይ ተካፍለዋል፡፡