በሳውዲ አረብያ የሚመራው ኅብረት በየመን ሁቲ አማጽያን ላይ ያደረሱትን የአየር ጥቃት ነፃ ምርመራ እንዲከፈትበት ተመድ ጠየቀ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በሳውዲ አረብያ የሚመራው ኅብረት በየመን ሁቲ አማጽያን ላይ ያደረሱትን የአየር ጥቃት ነፃ ምርመራ እንዲከፈትበት ተመድ ጠየቀ።
ሁቲ አማጽያኑ በአየር ጥቃቱ ቢያንስ ሃምሳ ሰዎች ተገድለዋል። ሰባ ሰባት ሰዎች ቆስለዋል የሚበዙት ህፃናት ናቸው ብለዋል።
አማጽያኑ እንዳሉት ከተተኮሱት ሚሳይሎች አንደኛው ልጆችን ከበጋ ወራት የሽርሽር ዝግጅት ወደቤት የሚመልስ አውቶብስ መቷል።
የተባበሩት መንግኅሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ ስለተካሄደው የአየር ጥቃት ነፃና ፈጣን ምርመራ እንዲከፈት ጠይቀዋል።