አዲስ አበባ —
ለአንድ ቀን ይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት በኢትዮጵያ የታዩ አዎንታዊ ለውጦችን ማድነቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።
የጽ/ቤቱ የፕሬስ ክፍል ኃላፊ ቢል ለኔ ስዩም ለጋዜጠኛች እንዳሉት ፕሬዚዳንቱ የስድስተኛውን ሃገራዊ ምርጫ እና የህዳሴውን ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ አድንቀዋል።
የውጭ ሃይሎች ኢትዮጵያ በገጠማት ውስጣዊ ፈተና ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንደሌለባቸው ፕሬዚዳንቱ መናገራቸውንም የፕሬስ ኃላፊዋ አስረድተዋል።
"እንደሁኔታው የማይለዋወጡና በወዳጅነታቸው የሚጸኑ እንደ ደቡብ ሱዳን ያሉ ወዳጆች በወሳኝ ጊዜያት እጅግ አስፈላጊ ናቸው" ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ናቸው በማህበራዊ ትስስር ገጽ ባሰፈሩት ፅሁፍ።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5