Your browser doesn’t support HTML5
በደቡብ አፍሪካ የቻይንኛ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
የቻይና የኮንፊዩሸስ ተቋማት በዓለም ዙሪያ የቻይና ቋንቋ ያስተምራሉ። ተቋማቱ የሚሰጡት ትምሕርት ቋንቋ ብቻ አይደለም። ከደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ከተማ በብዙ መቶ ኪሎ ሜትሮች ርቆ በሚገኝ ገጠራማ አካባቢ የተከፈተ ትምሕርት ቤት የጎበኘችው የአሜሪካ ድምጿ ኬት ባርትሌት ትምሕርት ቤቱ የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ትምህርትም ከቋንቋ ትምህርቱ ጋራ አቀናጅቶ እንደሚሰጥ ተመልክታ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።