የርዋንዳ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ፕረዚዳንት ፖል ካጋሜ እአአ እስከ 2034 ዓ.ም. በስልጣን እንዲቆዩ የሚያስችል የህገ-መንግስት ማሻሻያ ሃሳብን አጽድቀዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የርዋንዳ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ፕረዚዳንት ፖል ካጋሜ እአአ እስከ 2034 ዓ.ም. በስልጣን እንዲቆዩ የሚያስችል የህገ-መንግስት ማሻሻያ ሃሳብን አጽድቋል።
ምክር ቤቱ ዛሬ የተሰጠውን ድምጽ ያጸደቀው በሙሉ ድምጽ ነው። የውሳኔው ሃሳብ ብሄራዊ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለህዝበ-ውሳኔ የሚቀርብ ሲሆን በቀላሉ ድጋፍ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
እድሜያቸው 58 የሆነው ፕረዚዳንት ካጋሜ ሰራዊታቸው እአአ በ 1994 አም በሀገሪቱ ሲፈጸም የቆየውን ፍጅት አብቅቶ ጽንፈኛ ሁቱዎችን ከስልጣን ካስወገደበት ጊዜ አንስቶ በስልጣን ላይ እንደሚገኙ የሚታወቅ ነው።
አሁን ባለው የሀገሪቱ ህገ-መንግስት መሰረት የሁለተኛ ጊዜ ስልጣናቸው እአአ በ 2017 አም ማብቃት አለበት። ይሁንና አሁን ህገ-መንግስቱ እንዲሻሻል በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት ለሌላ የሰባት አመታት የስልጣን ጊዜ ለመወዳደር ይችላሉ። ከዚያ በኋላ ደግሞ ለሁለት የአምስት አመታት የስልጣን ጊዜ ሊወዳደሩ ይችላሉ።
የርዋንዳ የህግ መምሪያ ምክር ቤት በያዝነው ወር ቀደም ሲል የውሳኔውን ሃሳብ አጽድቋል። ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።
የርዋንዳ ዲሞክራያዊ አረንጓዴ ፓርቲ የተባለው ተቃዋሚ ድርጅት የህገ-መንግስቱ ማሻሻያ “ለዘላቂ ሰላማና ጸጥታ” ተግዳሮት ይሆናል ሲል ነቅፏል።
Your browser doesn’t support HTML5