በሩሲያ እስረኞች የእስር ቤቱን ሠራተኞች አገቱ

ደቡባዊ ቮልጎግራድ ክልል

ደቡባዊ ቮልጎግራድ ክልል

በደቡባዊ ቮልጎግራድ ክልል ለብቻው ተነጥሎ በተሰራ ወህኒ ቤት ውስጥ የሚገኙ አስረኞች፥ የእስር ቤቱን ሠራተኞች ዛሬ አርብ አግተው መውሰዳቸውን የማረሚያ ቤት ባለሥልጣናት ተናገሩ።

ባለሥልጣናቱ ከሰኔ ወር ወዲህ በሩሲያ እስር ቤት ውስጥ ይህ ዓይነቱ ክስተት ሲፈፀም ሁለተኛው ነው ብለዋል።

የሩሲያ ፌዴራል ማረሚያ ቤት ባወጣው መግለጫ "ወንጀለኞቹ የ (IK-19) የማረሚያ ተቋም ሠራተኞችን አግተው ወስደዋል" ብሏል።

በአሁኑ ጊዜ "ታጋቾቹን ለማስለቀቅ እርምጃዎች እየተወሰዱ ሲሆን በሂደቱም ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አሉ" ሲል መግለጫው ማመልከቱን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡