ሚቀጥለው ወር በሩስያ መሪነት ሶቺ ላይ የሚከፈተው የሶሪያ ሰላም ድርድር ከሶሪያ ሕዝብ ሰፊ ድጋፍ ያለው መሆኑን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሚሸመግለው የሰላም ሂደት መሰረት እንደሚጥል የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ተናገሩ።
በሚቀጥለው ወር በሩስያ መሪነት ሶቺ ላይ የሚከፈተው የሶሪያ ሰላም ድርድር ከሶሪያ ሕዝብ ሰፊ ድጋፍ ያለው መሆኑን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሚሸመግለው የሰላም ሂደት መሰረት እንደሚጥል የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ተናገሩ።
ላቭሮቭ ይህን የተናገሩት አርባ የሶሪያ ሽምቅ ተዋጊ ቡድኖች እንድ ላይ ሆነው በወሰዱት አቋም ሩስያ የመንግሥታቱን ድርጅት የሰላም ሂደት በብልጠት ለማደናቀፍ እየሞከረች ናት ብለው በመወንጀል በሶቺው ጉባዔ ላይ አንካፈልም ካሉ በኋላ ነው።
ሩስያ የምትፈልገው ፕሬዚደንት ባሻር አል አሳድ ከሥልጣን ይውረዱ የሚለውን ጥያቄያችንን ለማስሰረዝ ነው ሲሉ አማፅያኑ ከሰዋል።
በሰላም ድርድር የሚሸመግል ከወገንተኝነት ነፃና ሃቀኛ ሊሆን የሚገባው ሆኖ ሳለ የሶሪያ መንግሥት ከማናቸውም ኃይለኛ ደጋፊ የሆነችው ሩስያ ግን አይደለችም ብለዋል አማፅያኑ፡፡