ዚምባቡዌ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት ከሩሲያ እና ከዓለም አቀፍ የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ድርጅት ጋራ በመሥራት ላይ ነች 

  • ቪኦኤ ዜና

የዚምባቡዌ መንግሥት ሀገሪቱ ያለባትን ሥር የሰደደ የኢሌክትሪክ ኃይል እጥረት ለማስወገድ የኒውክሌየር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ለዚህም ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ተቆጣጣሪ ድርጅት እና ከሩሲያዊያን መዋዕለ ነዋይ መዳቢዎች ጋራ በመሥራት ላይ መሆኑን አስታውቋል።

Your browser doesn’t support HTML5

ዚምባቡዌ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት ከሩሲያ እና ከዓለም አቀፍ የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ድርጅት ጋራ በመሥራት ላይ ነች 

ኮለምበስ ማቩንጋ ከሃራሬ ባጠናቀረው ዘገባ፣ ዚምባቡዌ እየደጋገመ የሚከሰተው ድርቅ ከውሃ የሚመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል እያዳከመው በመኾኑ ከነፋስ እና ከጸሐይ ኃይል በርከት አድርጋ ለማመንጨት የምትችልበትን መንገድ በማጥናት ላይ ነች፡፡