ሩሲያ አሜሪካዊውን የዎል ስትሪት ጀርናል ሪፖርተር ኤቨን ገርሽኮቪች ስለላ ፈጽሞብናል በሚል የ16 ዓመት ቅጣት አስተላልፋለች፡፡ ዎል ስትሪት ጀርናል እና አሜሪካ ክሱን ያስተባብላሉ።
የክስ ሂደቱ መቋጫ ማግኘቱ በሞስኮ እና በዋሽንግተን መካከል የእስረኞች ልውውጥ እንዲደረግ ጥርጊያ መንገድ ይከፍታል ተብሏል።
ጀርናሉ የፍርድ ሂደቱን “አሳፋሪ እና የይምሰል” ሲል ገልጾታል።
ፀጉሩን ተላጭቶ በፍርድ ቤቱ የተገኘው ኤቨን ገርሽኮቪች መረጋጋት ይታይበት ነበር ተብሏል።
በዳኛው የተባለው ገብቶት እንደሆነ የተጠየቀው ጋዜተኛ፣ የአዎንታ መስል ሰጥቷል።
ውሳኔው በፍርድ ቤቱ በንባብ ከተሰማ ብኋላም፣ “ኤቨን እንወድሃለን” ሲል አንድ ሰው በጩክት እንዳሰማ ታውቋል።
የፍርድ ሂደቱ የተካሄደው በዝግ ሲሆን፣ ውሳኔው በሚነበብበት ጊዜ አልፎ አልፎ ፈገግ ሲል ተስተውሏል። ባለፈው ዓመት መ ቢት በሩሲያ የተያዘው ኤቨን ገርሽኮቪች እስከ ዛሬ 478 ቀናትን በእስር አሳልፏል።
ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን፣ ኤቨን ገርሽኮቪች በሪሲያ መንግስት ኢላማ የተደረገው “ጋዜጠኛ እና አሜሪካዊ ስለሆነ ነው” ብለዋል።