ሩሲያ የዩክሬን ትልቁን የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫን ጨምሮ በአገሪቱ የሚገኙ በርካታ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ማሰራጫዎች ላይ ጥቃት ሰንዝራለች፡፡
በጥቃቱ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጥ በሰፊው ሲከሰት፣ አምስት ሰዎችም ተገድለዋል።
በጥቃቱ ከ60 በላይ ድሮኖችና 90 የሚሆኑ ሮኬቶች ጥቅም ላይ መዋላቸውን የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ዛሬ ዓርብ አስታውቀዋል።
አንድ ቀን ቀደም ብሎም ሩሲያ የዩክሬን መዲና ኪቭን በ31 ሚሳዬሎች ደብድባለች፡፡
ጦርነቱ ከጀመረ አንስቶ በዩክሬን የኤሌክትሪክ ኃይል ላይ የተፈፀመ ከባዱ ጥቃት መሆኑን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
ሩሲያ በአየር የምትፈጽመው እያንዳንዱ ከባድ ጥቃት የዩክሬንን የመከላከል አቅም እያዳከመው መሆኑ በመነገር ላይ ነው።
ከአሜሪካ ለዩክሬን ሊሰጥ የታሰበው ወታደራዊ ዕርዳታ ጊዜ በመውሰድ ላይ ሲሆን፣ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌኒስኪ ምዕራባውያን አጋሮቻቸው ተጨማሪ የጦር መሣሪያዎችን እና ተተኳሾችን እንዲረዱ በመወትወት አይ ናቸው።
የሩሲያ ጥቃት ዲንፕሮ በተሰኘው የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ላይ የእሳት አደጋ ያስክትለ ሲሆን፣ ሃይል ማመንጫው ዛፕሮዤዢያ ለሚገኘው እና በአውሮፓ ትልቁ የኑክሌር ማመንጫ ጣቢያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያቀብል እንደነበር ታውቋል።