ገዥው ፓርቲና መንግሥት ለመደራደር የወሰኑት ከፍርሃትና ከውጭ ኃይሎች ጫና በመነጨ ምክንያት አለመሆኑን ጠ/ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሰሞኑን ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባ —
ገዥው ፓርቲና መንግሥት ለመደራደር የወሰኑት ከፍርሃትና ከውጭ ኃይሎች ጫና በመነጨ ምክንያት አለመሆኑን ጠ/ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሰሞኑን ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል፡፡ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ከዚህ አንፃር ያላቸው አረዳድ የተሳሳተ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
“የውጭ ኃይል” የሚል አገላለፅ አለመጠቀማቸውን የተናገሩ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው፣ መንግሥትና ገዥው ፓርቲ ለመደራደር የወሰኑት በሕዝቡ ጫና እንደሆነ ግን አስታውቀዋል፡፡
አደባባይ የወጣው፣ በፓርላማም የተነገረው፤ ገዥው ፓርቲና ሃያ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እያካሄዱት ባሉት የቅድመ ድርድር ውይይት ያከራከረው ሃሳብ ነው፡፡ የመንግሥታቸውን የስድስት ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት ሰሞኑን ለፓርላማ ያቀረቡት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝም ጉዳዩን የሪፖርቱ አካል አድርገዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5