በአማራ ክልል ተመላሽ ፍልሰተኞች ለዳግም ፍልሰት መዳረጋቸውን ገለጹ

ደሴ

Your browser doesn’t support HTML5

በአማራ ክልል ተመላሽ ፍልሰተኞች ለዳግም ፍልሰት መዳረጋቸውን ገለጹ

ከተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ወደ አማራ ክልል ተመልሰው የነበሩ ሰዎች ለዳግም ፍልሰት መዳረጋቸውን ተናገሩ። ቪኦኤ ያነጋገራቸው፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ የሚገኙ ከስደት ተመላሾች፣ መንግሥት ሊያቋቁማቸውን የገባውን ቃል ባለመጠበቁ፣ በድጋሚ ለመሄድ ዝግጅት ላይ መኾናቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ተንቀሳቅሰው መሥራት አለመቻላቸው ችግሩን እንዳባባሰው ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ ከክልሉ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚደረገው ፍልሰት መባባሱን አረጋግጦ፣ ተመላሾችን ለማቋቋም የአቅም ውስንነት መኖሩን አስታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያይዘው ፋይል ይከታተሉ።