ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከካይሮ ተመለሱ

  • ቪኦኤ ዜና
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ልዑካቸው ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ወደ አገራቸው ተመለሱ

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ልዑካቸው ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ወደ አገራቸው ተመለሱ

በግብፅ የሦስት ቀናት ይፋ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ልዑካቸው ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የኤርትራው የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል ኤክስ በተሰኘው የማኅበራዊ መልዕክት መለዋወጫ ገጽ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አመለከቱ።

ፕሬዝዳንቱ በቆይታቸው ከግብጹ አቻቸው ጋር ምክክር ካደረጉባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች የሁለትዮሽ የትብብር ግንኙነታቸውን ማጠናከር፣ የሱዳኑን ግጭት፣ የቀይ ባህርን የደህንነት ይዞታ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ያካተተ ነበር ብለዋል።