Your browser doesn’t support HTML5
ዓለምአቀፍ ጉዞ ላይ ሳሉ ከየመን ዋና ከተማ ሰንዓ አይሮፕላን ጣቢያ ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያ የተወሰዱትና አሁን እሥር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲለቀቁ ለማድረግ እየጣረ መሆኑን ሪፕሪቭ የሚባለው ድርጅት ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡
የሞት ፍርደኞችን ለማገዝና ለመደገፍ የሚሠራው ዓለምአቀፍ ግብረሠናይ ድርጅት ዳይሬክተር ማያ ፎ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “አንዳርጋቸው የታሠሩት ሕገወጥ በሆነ መንገድ ነው፤ ወደ ኢትዮጵያ ተጠልፈው የተወሰዱትም በሕገወጥ ሁኔታ ነው ብለን ነው የምናምነው” ብለዋል፡፡
የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዘፈቀደ እሥራቶች ተከታታይ ቡድን እየተከታተለ መሆኑንና እሥራቱ በዘፈቀደ የተፈፀመና ሕገወጥም መሆኑን በመጠቆም እንዳለቀቁ መጠየቁን፣ የድርጅቱ የሥቃይ አያያዝ ወይም ቶርቸር ጉዳዮች ልዩ ራፖርተርም ስለዚሁ ጉዳይ ለኢትዮጵያም ለእንግሊዝ መንግሥትም አንዳርጋቸው በሥቃይ የመያዝ አደጋ ስላለባቸው እዚያ ተይዘው መቆየት እንደሌለባቸው አሳስበው ደብዳቤ መፃፋቸውንና የአፍሪካ ኅብረትም ጉዳዩን እየተከታተለው መሆኑን ማያ ፎ ገልፀዋል፡፡
ለተጨማሪ ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡