በየመን የሁቲ አማጺያን የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ሰራተኛን አሰሩ

  • ቪኦኤ ዜና

የየመን ሁቲ አማጺያን በአሁኑ ሰዓት ሥራ ባቆመው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ውስጥ ይሰሩ የነበሩ አንድ የቀድሞ ባለሥልጣን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ታውቋል።

በአማጺያኑ እጅ የሚገኙ የቀድሞ የኤምባሲው ሠራተኞች ቁጥር 11 ደርሷል፣ እንደ የመን ባለሥልጣናት ቆጠራ ከሆነ።

ዋና ከተማዋ ሰንዓ እና የሃገሪቱን አብዛኛ ሰሜናዊ ክፍል የተቆጣጠሩት፣ በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማጺያን የቀድመውን የኤምባሲው የፕሬስ ባለሥልጣን በቁጥጥር ስር ያዋሏቸው ባለፈው ሳምንት እንደሆነ የመብት ተሟጋቹ ጠበቃ አብደል ማጂድ ሳብራ እና ማንነታቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የታሳሪ ቤተሰቦች ተናግረዋል።

ባለሥልጣኑ በሁቲዎች የደኅነነት እና ሥለላ ተቋም ግቢ ውስጥ እንደሚገኙ፣ ባለሥልጣኑም ይሁን ሌሎች ታሳሪዎች ላይ ክስ ተከፍቶ እንደሁ የሚታወቅ ነገር አለመኖሩን ሳብራ አክለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ይች ጉዳይ መስሪያ ቤት ለአሶሼትድ ፕረስ በጻፈው ደብዳቤ፣ በሀገሪቱ ውስጥ ኗሪ የሆኑ የቀድሞው የኤምባሲ ሰራተኞችን ለማስፈታት ያልተቋረጠ ጥረት እየተደረገ ነው።

ዋሺንግተን በየመን የሚገኘውን ኤምባሲዋን የዘጋችው ሀገሪቱ በጦርነት መፈረካከስ በጀመረችበት የአውሮፓዊያኑ 2015 ዓም ነው። ዘገባው የአሶሼትድ ፕረስ ነው።