የእምነት ተቋማትና የኃይማኖት አባቶች በደሴ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ ውሎ ሀገረስብከት ሀገራዊ የሰላምና የአንድነት ጉባዔ

"ሁሉ ነገር ድሮ ቀረ" የሚሉ ወገኖች አጥብቀው ከሚሟገቱባቸው አጀንዳ ውስጥ ቀዳሚው የግብረገብነት ጉዳይ ነው፡፡

"ግብረገብነት እየተናደ፣ የተውሶ ባህል ማንነታችንን እየቦረቦረ ሄደ" ይላሉ፡፡ ይህ አስተሳሰብ አድማሱን አስፍቶ በአዲስ ገፅታ መንፀባረቅ ጀምሯል፡፡

"ግብረ ገብነት በተሸረሸረበት ትውልድ ውስጥ አገራዊ ተቆርቋሪነት ይኮስሳል፤ ምክንያታዊ አስተሳሰብ ይጠፋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ቀዳሚ ተጠያቂዎቹ የኃይማኖት አባቶች ናቸው" የሚሉ አስተያየቶች እየተሰሙ ነው፡፡

"የእምነት ተቋማትና የኃይማኖት አባቶች የድርሻቸውን አለመወጣት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ለሚስተዋሉ መሠረተ-ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ድርጊቶች መከሰት ምክንያት ነው" ሲሉ ይሚሟገቱ ብዙ ናቸው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

Your browser doesn’t support HTML5

የእምነት ተቋማትና የኃይማኖት አባቶች በደሴ