ዋናው ጉዳይ የሰዎች መፈታት አይደለም - አቶ ጥሩነህ ገምታ /ኦፌኮ/

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ

ከገዥው ፓርቲና ከመንግሥት የሚጠበቀው “የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና መፈታት ሳይሆን ለሕዝብ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ነው” ሲሉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጥሩነህ ገምታ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ተናግረዋል።

ከገዥው ፓርቲና ከመንግሥት የሚጠበቀው “የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና መፈታት ሳይሆን ለሕዝብ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ነው” ሲሉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጥሩነህ ገምታ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ተናግረዋል።

‘ዋና’ የሚሏቸውን ጉዳዮች አቶ ጥሩነህ ሲዘረዝሩም “የዴሞክራሲ ምኅዳሩ መስፋት፣ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ የሚሣተፉበት ሥርዓተ-መንግሥት መመሥረት፣ መልካም አስተዳደርን የሚያጎድሉና ሙሰኛ የሆኑ ሰዎች ለሕግ መቅረብ፣ ሦስቱም የመንግሥት አካላት እራሣቸውን በቻሉበት ሁኔታ መደራጀት ይኖርባዋል” ብለዋል።

አቶ ጥሩነህ አክለውም “ሌሎች ኃይሎችም በነፃነት መንቀሳቀስ እንዲችሉ፣ በሃገሪቱ ላይ ጥቂቶች ክንዳቸውን የሚያሳዩበት ጊዜ ማብቃት እንደሚኖርበት፣ የምርጫ ኮሚሽኑ እንደገና እንዲዋቀር ያስፈልጋል”

“ሕገመንግሥቱንና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን ሥራ ላይ ለማዋል ሥራው እንደአዲስ መጀመር አለበት” ብለዋል የኦፌኮው የሥራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጥሩነህ ገምታ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ዋናው ጉዳይ የሰዎች መፈታት አይደለም - አቶ ጥሩነህ ገምታ /ኦፌኮ/