ዓለም አቀፉ ህብረተሰብ አብዛኛውን ትኩረቱን በሶርያ ላይ በማድረጉ በኢትዮጵያ በሚገኙት የጎረቤት ሃገሮች ስደተኞች ላይ ተፅእኖ ማሳደሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቢሮ ቃል አቀባይ ተናገሩ።
አዲስ አበባ —
የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቃል አቀባይ አቶ ክሱት ገብረ-እግዜብሄር ለአሜሪክ ድምጽ ሬድዮ እንደተናገሩት አገሪቱ ከ 700,000 በላይ ስደተኞችን በተለያዩ ካምፖች እያስተናገደች ነው።
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ቀን ከነዚህ አንዱ በሆነው አሶሳ አከባቢ በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ሲከበር በኢትዮጵያ የሚገኙ የጎረቤት ሃገሮች ስደተኞች ቁጥር እንዴት እየጨመር እንደመጣ ተመልክቷል።
የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ክሱት ገብረ-እግዜብሄር ጋር የተካሄደው ቃለ-ምልልስ የመጀመርያ ክፍል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን ዛሬ በመላው አለም ታስቦ ውሏል
የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ክሱት ገብረ-እግዜብሄር ጋር የተካሄደው ቃለ-ምልልስ ሁለተኛ ክፍል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን ዛሬ በመላው አለም ታስቦ ውሏል(ክፍል 2)