በሶማሊያ በዓለምቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የምትሰራ ነርስ ተጠለፈች

  • ቪኦኤ ዜና
በዓለምቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የምትሰራ ነርስ በሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ ውስጥ መጠለፍዋን ድርጅቱ አረጋገጠ።

በዓለምቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የምትሰራ ነርስ በሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ ውስጥ መጠለፍዋን ድርጅቱ አረጋገጠ።

የቀይ መስቀል ኮሚቴው የሶማልያ መልዕክተኞች ምክትል ኃላፊ ዳኔል ኦማሊ የባልደረባችን ደኅንነት ጉዳይ እጅግ አሳስቦናል” የሚል መግለጫ አውጥተዋል። ሶማልያ ውስጥ እጅግ በከፋ ሁኔታ የሚኖሩትን ሰዎች ህይወት ለማትረፍና ጤንነታቸው እንዲጠበቅ ቀንና ሌሊት ስትጥር የቆየች ነርስ ናት ሲሉም አክለዋል።

ሰንጃ ኒንቲት የተባለችው ጀርመናዊት ነርስ የተጠለፈችው ከዓለምቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ቅጥር ጊቢ መሆኑን የሶማልያ የፀጥታ ደኅንነት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዐብዱል ዐዚዝ ዐሊ ኢብራሂም ጠቁመዋል።