በሀገሪቱ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ከስሜታዊነት መውጣት፣ አስተውሎ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ተባለ

  • እስክንድር ፍሬው
አሁን በሀገሪቱ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ከስሜታዊነት መውጣትንና አስተውሎ መንቀሳቀስን የሚጠይቅ መሆኑን የሁለት ዋና ዋና የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች አስታወቁ፡፡

አሁን በሀገሪቱ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ከስሜታዊነት መውጣትንና አስተውሎ መንቀሳቀስን የሚጠይቅ መሆኑን የሁለት ዋና ዋና የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች አስታወቁ፡፡

አንዳንድ ትንኮሳዎች ቢኖሩ እንኳን በቶሎ ምላሽ መስጠት እንደማያስፈልግ ለአባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን መመሪያ ሰጥተናል ያሉት የኦነግ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ ናቸው፡፡ ሰልፍና ስብሰባ የሚካፈሉ ወጣቶች የሌላውን መብት ከሚኩና ከሚያንቋሽሹ እንደዚሁም ግጭት ከሚቀሰቅሱ፣ መፈክሮችና ዘፈኖች እንዲጠነቀቁ የመከሩት ደግሞ የግንቦት 7 ቃል አቀባይ አቶ አበበ ቦጋለ ናቸው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

Your browser doesn’t support HTML5

በሀገሪቱ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ከስሜታዊነት መውጣት፣ አስተውሎ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ተባለ