Your browser doesn’t support HTML5
ባይደን የኳድ መሪዎችን ስብሰባ በመኖሪያ ቤታችው ያስተናግዳሉ
ፕሬዝደንት ባይደን በመጪው ቅዳሜ የአውስትራሊያ፣ ህንድና ጃፓን መሪዎችን በዋይት ሃውስ ተቀብለው “ኳድ” በሚል የሚታወቀዋን የአራቱን ሃገራት ቡድን ስብሰባ ያስተናግዳሉ። ቡድኑ በተለይም በኢንዶ ፓሲፊክ ቀጠና ባለ ስልታዊ የፀጥታ ትብብር ያተኩራል። ሕዝብ በብዛት የሚገኝበት ቀጠናው ለቻይናም ከኢኮኖሚ እና ከስልት አንጻር ወሳኝ ነው።
የቪኦኤ የዋይት ሃውስ ዘጋቢ አኒታ ፓወል የላከችው ዘገባ ነው።