በቆንዳላ ወረዳ የቀጠለው ግጭት የሕይወት እና የንብረት ጉዳት እያደረሰ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በቆንዳላ ወረዳ የቀጠለው ግጭት የሕይወት እና የንብረት ጉዳት እያደረሰ ነው

በምዕራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ወረዳ፣ በመንግሥት ታጣቂዎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል በቀጠለው ግጭት፣ ቢያንስ አንድ አርሶ አደር ሲገደሉ 15 ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ።

ለግድያው የመንግሥት ኀይሎችን ተጠያቂ ያደረጉት የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች፣ ዐማፂ ቡድኑን ይደግፋሉ፤ በሚል ባልታጠቁ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ጠቅሰው ወንጅለዋል።

ነዋሪዎቹ በሰነዘሩት ውንጀላ ላይ፣ ከምዕራብ ወለጋ ዞንና ከቆንዳላ ወረዳ አስተዳደር አካላት እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ይኹንና የኢትዮጵያ ጦር ኀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ከዚኽ ቀደም ለአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች በሰላማውያን ሰዎች እና በሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት አይፈጽሙም፤ ሲሉ የሚቀርቡ ክሶችን አጣጥለዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።