ኢትዮጵያን የሚጎበኙ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች በሚያደርጓቸው ንግግሮች “ስለሃገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ የተሳሳቱ ወይም የተዛቡ መልዕክቶችን ያስተላልፋሉ” ሲል የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ አስታውቋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ኢትዮጵያን የሚጎበኙ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች በሚያደርጓቸው ንግግሮች “ስለሃገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ የተሳሳቱ ወይም የተዛቡ መልዕክቶችን ያስተላልፋሉ” ሲል የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ አስታውቋል።
መድረክ አዲስ አበባ ለሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ይድረስ ባለው ሰሞኑን ባወጣው ግልፅ ደብዳቤ ላይ የቀደሙት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትና በቅርቡ ከሥራቸው የተነሱት ሬክስ ቲለርሰን ሁለቱም ወደ ኢትዮጵያ ኦፊሴላዊ ጉብኝቶችን ባደረጉባቸው ጊዜዎች “በአፍ ወለምታ” ሲል የጠራቸውን “የተሳሳቱ መልዕክቶች አሰምተዋል” ብሏል።
የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ግንኙቶች ተጠሪው ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ሙሉ ቃለምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5