በምዕራብ ወለጋ የተፈፀመው ብሄር ተኮር ግድያ ዓለማቀፋ ማኅበረሰብ እንዲያወግዝ ተጠየቀ

ባህር ዳር

ባህር ዳር

በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ዘር ተኮር ግድያ ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ እንደሚያወግዝ የክልሉ ገዥ ፓርቲ ጥሪ አቀረበ።

እየተፈጸመ ላለው ጥቃት ተጠያቂዎቹም ህወሓት እና ኦነግ ሸኔ ናቸው ብሏል የአማራ ብልፅግና ፓርቲ።

የህወሓት ትልቁ አጀንዳም ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው በማለት ነው የወነጀለው። የህወሓት እና የኦነግ ሸኔ አጀንዳ አስፈፃሚዎች ደግሞ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ጭምር እንደሚገኙ ጠቁሟል።

መንግሥት በመዋቅሩ ውስጥ የሚገኙትን እነዚህን አስመሳዮች በማጥራት ላይ እንደሚገኝም የአማራ ብልፅግና ፓርቲ አስታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

Your browser doesn’t support HTML5

በምዕራብ ወለጋ የተፈፀመው ብሄር ተኮር ግድያ ዓለማቀፋ ማኅበረሰብ እንዲያወግዝ ተጠየቀ