ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ስለአገር አድን የጋራ ንቅናቄ ይናገራሉ

  • ሰሎሞን ክፍሌ

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ /ፎቶ - ከፋይል የተወሰደ/

ኤርትራ ውስጥ የሚገኙ በትጥቅ ትግል ላይ እንደሚገኙ የሚገልፁ አራት ኢትዮጵያዊያን የተቃዋሞ ንቅናቄዎች ባለፈው ሰኞ፤ ጳጉሜ 2 ቀን 2007 ዓም የጋራ ንቅናቄ መመሥረታቸው ተዘግቧል።

Your browser doesn’t support HTML5

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ስለአገር አድን የጋራ ንቅናቄ ይናገራሉ

ኤርትራ ውስጥ የሚገኙ በትጥቅ ትግል ላይ እንደሚገኙ የሚገልፁ አራት ኢትዮጵያዊያን የተቃዋሞ ንቅናቄዎች ባለፈው ሰኞ፤ ጳጉሜ 2 ቀን 2007 ዓም የጋራ ንቅናቄ መመሥረታቸው ተዘግቧል።

የጋራ ንቅናቄውን የመሠረቱት አራት ድርጅቶች የአፋር ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ፥ የትግራይ ሕዝብ የጋራ ንቅናቄ፥ የአማራ ሕዝብ የጋራ ንቅናቄና የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ መሆናቸው ተገልጿል።

አራቱ ድርጅቶች በጋራ የመሠረቱትን አዲሱን ንቅናቄ፥ “አገር አድን የጋራ ንቅናቄ” ሲሉ ጠርተውታል።

“የኢትዮጵያ አገር አድን የጋራ ንቅናቄ” ሲመሠረትም ዶክተር ብርሃኑ ነጋን በዋና ሊቀመንበርነት፥ አቶ ሞላ አስገዶምን በምክትል ሊቀመንበርነት የመረጠ ሲሆን ከአራቱም አባል ድርጅቶች የተውጣጣ አገር አድን ሠራዊት መቋቋሙም ተገልጿል።

ድርጅቶቹ የጋራ ንቅናቄውን በምን መልክ ነው የፈጸሙት? በውኅደት መልክ የተፈጸመ ነው? ውኅደት ካልተፈፀመ ደግሞ የሎጂስቲክስና የአመራር ተግባራትን እንዴት አስማምቶ ማካሄድ ይቻላል?

ሰሎሞን ክፍሌ እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን ይዞ የአገር አድን የጋራ እንቅስቃሴውን ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ካሉበት አካባቢ በስልክ አነጋግሯል።

ቃለ-ምልልሱን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡