ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም ስለዲያስፖራ ትረስት ፈንድ

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም /ፎቶ ፋይል/

ዐሥራ አምስት አባላት ያሉት የዴያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት አባላት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ጥሪ ተቀብለው በበጎ ፈቃደኝነት ለማገልገል የተሰባሰቡ እንደሆኑ የአማካሪ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የ2011O ዓ.ም በጀትን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በቀን አንድ ዶላር ከአንድ ማኪያቶ ላይ ቀንሰው በኢትዮጵያ የሚገኙ ዜጎችን እንዲረዱ ያቀረቡት ሐሳብ ተቀባይነትን አግኝቶ ዐሥራ አምስት አባላት ያሉት የዴያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት አባላት ተመርጠዋል።

የንግድና ምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች የታማኝነት ወይም የባላደራ ገንዘብ የሚል ስያሜን የሚሰጡት ትረስት ፈንድ የድጋፍ ገንዘብ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይህንን ገንዘብ ቢለግሱ አንድም ሳንቲም ሳትወድቅ ሳትጠፋ በሀገሪቱ የሚታዩ ማኅበረሰባዊ የልማት ክፍተቶችን ለመሙላት እንደሚውል አረጋግጠዋል።

ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ የተቀበሉ፤ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ በከፍተኛ ባለሞያነት የሚሰሩ፣ በታዋቂ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ተመራማሪዎችና ፕሮፌሰሮች፣ ዝነኛ በሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚያገለግሉ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትን በሰብዓዊ መብት ጥሰት አብዝተው በመተቸት ከሚታወቁት የመብት አራማጆች በአጠቃላይ 15 ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን ይህን ሥራ በበጎ ፈቃድ ለማከናወን መወሰናቸው ይፋ ተደርጓል።

ትረስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት አባላት በተመለከተ በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሳንበርናዲኖ የፖለቲካ ሳይንስ መምሕርና የሕግ ባለሞያና ሰብሳቢውን ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያምን አነጋግረናቸዋል።

(ዝርዝሩን ከታያይዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)