በደሴ ከተማ በኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ

ከ1ሰላሣ ሚሊዮን ብር በላይ ለግንባታ፣ ለመሣሪያዎችና ለግብአቶች ወጭ አድርገው በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አጥረት ምክንያት ወደ ሥራ መግባት አለመቻላቸውን በደሴ ከተማ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሠማራት እንቅስቃሴ የጀመሩ ግለሰቦች ገልፀዋል።

ባለሃብቶቹ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በብድር ከባንክ ወስደው ሥራ ባለመጀመራቸው ለተጨማሪ ኪሣራ መዳረጋቸውንም ይናገራሉ።

የአማራ ክልል መንግሥት እንደ ኢንቨስትመንት ዘርፎቹ ዓይነት እየታየ የኃይል አቅርቦት ጥያቄውን በቅደም ተከተል ለመመለስ እንደሚጥር አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሥሪያ ቤት ግን ችግሩን ለመፍታት ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እንዳለበት እየተናገረ ነው።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በደሴ ከተማ በኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ