ማዳጋስካር ከእሥር ቤት ለማምለጥ የሞከሩ ተገደሉ

  • ቪኦኤ ዜና

ማዳስጋስካር ውስጥ ትናንት ፋራፈንጋና ከተባለው እሥር ቤት ለማምለጥ የሞከሩ ሃያ እስርኞች፣ በተከፈተባቸው ተኩስ እንደተገደሉ፣ ስምንት ታራሚዎች ደግሞ እንደቆሰሉ ታውቋል። ሦላሳ ሰባት እስረኞች ተይዘው ሦላሳ አንድ ደግሞ ማምለጣቸውን ባለሥልጣናቱ ጠቁመዋል።

ማዳጋስካር እሥር ቤት ውስጥ የገቡ ሰዎች፣ ክስ ሳይመሰረትባቸው ለዓመታት ያህል ሊቆዩ እንደሚችሉና ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙት ይልቅ፣ ክስ ያልተመሰረተባቸው እንደሚበዙ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት፣ በባለፈው ዓመት ባወጣው ዘገባ ጡቁሟል።