በአዲስ አበባ ከታሰሩ ወጣቶች ፍ/ቤት ያልቀረቡ መኖራቸውን ጠበቆች ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

በአዲስ አበባ ከታሰሩ ወጣቶች ፍርድ ቤት ያልቀረቡ መኖራቸውን ጠበቆች ገለጹ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ከታሰሩ ሰዎች መካከል እስካሁን ፍርድ ቤት ያልቀረቡና በእስር ላይ የሚገኙ መኖራቸውን ጠበቆች ገለጹ።

ከፍርድ ቤት የዋስትና ውሳኔ ውጭ በእስር ላይ የቆዩት ፓስተር ቢኒያም ሽታዬ ደግሞ ትላንት ምሽት ላይ መፈታታቸውን የቤተክርስቲያኗ በጎ ፈቃደኞች የሕግ ቡድን አባል ጠበቃና የሕግ አማካሪ ብሩክ ደረጀ ተናግረዋል፡፡

በሌላ ዜና፣ ከአድዋ ክብረበዓል አከባበር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች መካከል የሚዲያ ባለሞያ አቤል ገብረኪዳን ከሕግ ውጭ በቁጥጥር ስር መዋሉንና ከአንድ ሳምንት በኋላ ፍርድ ቤት መቅረቡን ጠበቃው አንዱዓለም ቡኬቶ ገልጸዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንዲሁም ከአድዋ ክብረ በዓል ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችን በተመለከተ ያሉ ዝርዝር ጉዳዮችን በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገልጿል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።