"የኅዳሴውን ግድብ ግንባታ የሚያቆም ምንም ኃይል የለም" - ጠ/ሚ ዐብይ

  • እስክንድር ፍሬው
የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ

የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ

በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ከግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጋር እንደሚናጋገሩ የገለፁት የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የኅዳሴውን ግድብ ግንባታ የሚያቆም ምንም ኃይል የለም ብለዋል፡፡

በአንዳንድ የግብፅ ወገኖች የሚንፀባረቀውን የኃይል አማራጭ ጉዳይ በተመለከተም፣ እንዋጋ ከተባለ ብዙ ሚሊዮን እናሰልፋለን፣ ውጤቱ ግን ማንንም አይጠቅምም ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ በዛሬ የፓርላም ማብራሪያቸው በሀገር ሰላምና ኅልውና ላይ አደጋ የደቀኑ ላሏቸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃንም ጠበቅ ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡

“አማረኛም ብትናገሩም፤ ኦሮምኛ ብትናገሩም፣ ዕርምጃ መውሰዳንችን አይቀርም" ነው ያሉት፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

"የኅዳሴውን ግድብ ግንባታ የሚያቆም ምንም ኃይል የለም" - ጠ/ሚ ዐብይ