ዛሬ ልዩ ስብሰባ ያካሄደው የኢትዮጵያ ፓርላማ አዲሱን የኢህአዴግ ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አህመድን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሰይሟል፡፡
አዲስ አበባ —
ዛሬ ልዩ ስብሰባ ያካሄደው የኢትዮጵያ ፓርላማ አዲሱን የኢህአዴግ ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አህመድን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሰይሟል፡፡ ይህ የስልጣን ሽግግር አዲስ ምዕራፍ የሚጀመርበት መሆኑን የገለፁት ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡ ወቅታዊውን ሁኔታም በተመለከትም፣ በተለያየ ጊዜ መስዕዋትነት ለከፈሉ፣ የመብት ተከራካሪዎች፣ ፖለቲከኞችና ታዳጊዎች መሞት ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ከሀገር ውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውለደ ኢትዮጵያውያን ባስተላለፉት መልዕክትም፣ በብሄራዊ መግባባት ወደ ቀጣይ ብሩህ ሀገራዊ ምዕራፍ እንሸጋገር ሲሉ ጥሪ አቅረበዋል፡፡
የአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ንግግር ዘመናዊ የንግግር መሥፈርቶችን ያሟላ፣ እንዲሁም የጋባዥነትና የአስታራቂነት ያለው ነው ሲሉ የፓርላማ አባላት እና ምሁራን ሌሎች አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5