Your browser doesn’t support HTML5
የፕሬዝዳንታዊው ክርክር ትረምፕ እና ሄሪስ የሰላ ትችት ተሰናዝረዋል
በኅዳር ወር በሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚፎካከሩት የሪፐብሊካን ፓርቲው እጩ ዶናልድ ትረምፕ እና የዲሞክራቲክ ፓርቲው ተፎካካሪያቸው ካመላ ሄሪስ ትላንት ማክሰኞ ምሽት በኤቢሲ ቴሌቭዢን አስተናጋጅነት በቴሌቭዥን ክርክር አካሂደዋል፡፡
ኢሚግሬሽን ጽንስ ማስወረድ እና የውጭ ፖሊሲን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ በብርቱ ተከራክረዋል፡፡ የፔንሲልቬኒያዋ ፊላዴልፊያ ከተማ ውስጥ የተካሄደውን የሁለቱን እጩ ተፎካካሪዎች የመጀመሪያ ክርክር የተከታተለው የአሜሪካ ድምጹ ስቲቭ ኸርማን ያስጠናቀረው ዘገባ እንዲህ ተመልክቶታል፡፡