የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በሃይለኛ ዝናብ አዘል ማዕበል አርማ
ወደተመታችው ፍሎሪዳ ክፍለ ሃገር ተጉዘዋል። በዚያም ስለተያዘው የመልሶ ማቋቋምና ጥረት ገለጻ ይደረግላቸዋል። ጉዳት ከደረሰባቸው አንዳንድ ነዋሪዎች ጋር ይነጋገራሉ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በሃይለኛ ዝናብ አዘል ማዕበል አርማ
ወደተመታችው ፍሎሪዳ ክፍለ ሃገር ተጉዘዋል። በዚያም ስለተያዘው የመልሶ ማቋቋምና ጥረት ገለጻ ይደረግላቸዋል። ጉዳት ከደረሰባቸው አንዳንድ ነዋሪዎች ጋር ይነጋገራሉ።
ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ ከፕሬዚደንቱ ጋር አብረው ተጉዘዋል። ፕሬዚደንቱ ወደ በፍሎሪዳ ጉብኝታቸው ወደ ፎርት ማይርስ እና ኔፕልስ ከተሞች እንደሚደርሱ ታውቋል።
ኤርማ በምዕራብ ፍሎሪዳ ሃይለኛ ዝናብ አዝሎ በከፍተኛ ንፋስ ሲነጉድ በሁለቱ ከተሞች በኩል ሲያልፍ በከባድ ጎርፍ እጥለቅልቁዋቸዋል።
ፕሬዚደንቱ ፍሎሪዳን ቀደም ብለው “አደጋ ውስጥ ያለ አካባቢ” ብለው አውጀዋል። ያም ከፌደራሉ መንግሥት በፍጥነት የዕርዳታ ገንዘብ እንዲልቀቅ ያግዛል፣ በተጎዱት አካባቢዎች የመልሶ ማቋቋም ጥረቶች ተጀምረዋል።
ባለሥልጣናት ጥረቱ ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ አስጠንንቀዋል፡፡