የትረምፕ ንግግርና የዓለም ምላሽ

  • ቪኦኤ ዜና

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ለተወካዮች ምክር ቤቱ የመጀመሪያውን ንግግራቸውን ባደረጉበት ወቅት

ክፍፍል የሚታይባት ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካዊ የተሃድሶ መንፈስ እንድትይዝ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ አሳስበዋል።

ፕሬዚደንቱ ትናንት ማታ ለተወካዮች ምክር ቤቱ የጋራ ስብሰባ ባሰሙት ንግግር የሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት ይዞታ እንዲያንችራራ፣ ድንበሮች እንዲጠበቁ፣ ወታደራዊ በጀት እንዲያድግና አጠቃላይ የጤና ጥበቃ እንዲጠናከር ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል።

ፕሬዚደንቱ ለምክር ቤት ያደረጉት የመጀመሪያ ንግግራቸው ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ የዓለም መሪዎች ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኮንግሬሱ ላደረጉት የመጀመሪያ ንግግር አስተያተቶቻቸውን እየሰጡ ነው።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዘዳንት አሜሪካ ለኔቶ ስላላት ቁርጠኝነትና በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ የንግድ ልውውጥ አሠራር የማስተዋወቅ እቅድ ስለ መኖሩም ተናግረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የትረምፕ ንግግርና የዓለም ምላሽ