ፕሬዚዳንት ትራምፕና ስደተኞች

  • ሔኖክ ሰማእግዜር
በዚህ ሳምንት በኦፊሴል ስራ የጀመሩት የዩናይትድ ስቴይትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በርካታ አዳዲስ መመሪያዎችን እያወጡ ነው፤ አስቀድመው በምረጡኝ ዘመቻቸው የሰጧቸው አስተያየቶችም ለተለያዩ ቡድኖች ስጋትና ተስፋ ሆነዋል።

በስደተኞችና ፍልሰተኞች የሚከተሏት የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በስደተኞችና ፍልሰተኞች ዙሪያ ምን አይነት ፖሊሲና አፈፃጸም እንደሚከተል ያሰጋቸው፤ የስደተኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስቀድመው መደራጀት ጀምረዋል።

የኦባማ አስተዳድር በርካታ ሰዎችን ጠርንፎ ወደ ሀገራቸው መላክ የጀመረውን ሥራ ትራምፕ ያስቀጥሉበታል ብለው ይጠብቃሉ።

በትናንትናው ዕለት የጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የዋይት ሃውስ ቤተ መንግሥት ቃል አቀባይ ሾን ስፓይሰር የፕሬዚዳንት ትራምፕ ቀዳሚ የኢምግሬሽን ፖሊሲ የሜክሲኮን ድንበር በግድግዳ አጥር መከለል ሲሆን የወንጀል ሪከርድ ያለባቸውን ደግሞ ወደ የሀገሮቻቸው መሸኘት ነው ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ፕሬዚዳንት ትራምፕና ስደተኞች