በቆቦ ከተማ ስለተገደለችው ነፍሰጡር አያንቱ እህቷ ትናገራለች

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በቆቦ ከተማ ትናንት ለሊት በጥይት ተመታ ተገድላ የተገኘችው የስድስት ወደ ነፍሰጡርና የአንድ ልጅ እናት አያንቱ መሐመድ አሟሟት አነጋጋሪ ሆኗል።

Your browser doesn’t support HTML5

በቆቦ ከተማ ስለተገደለችው ነፍሰጡር አያንቱ እህቷ ትናገራለች

እህቷ በከተማው ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን ለማስፈፀም ከተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል በአንዱ መገደሏን በአካባቢው የነበረ ሰው እንደነገራቸው ተናግራለች።

የአስክሬን ምርመራ ውጤቷ አያንቱ ጭንቅላቷን በሁለት ጥይት ተመታ መሞቷን እንደሚያሳይ የሕክምና ባለሞያዎች ገልፀዋል።

የከተማው ከንቲና በበኩላቸው በግድያው ከተጠረጠሩ መካከል አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል በቁጥጥር ስር መዋሉን ነግረውናል።

ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።