Your browser doesn’t support HTML5
ኒዠር በዲሞክራሲያዊ ሽግግር ዕቅድ ላይ የሚነጋገር ጉባዔ ልታካሂድ ነው
ኒዠር ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የቆየውን እና የዲሞክራሲያዊ ሽግግር ዕቅድ ላይ የሚያተኩረውን ጉባዔ በመጪው ሳምንት ታካሂዳለች።
እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2023 ሐምሌ ወር ፕሬዝደንት መሐመድ ባዙምን በመፈንቅለ መንግሥት የገለበጧቸው ጄኔራል አብዱራሃማኔ ቺያኒ፣ ውይይቱ አሳታፊ እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው አስተዳደራዊ ጉዳዮችን የሚለይ እንደሚሆን ተናግረዋል። ሽግግሩ የሚከናወንበትን የጊዜ ሰሌዳም ያዘጋጃል ብለዋል።
ከአቡጃ ቲመቲ ኦቢዬዙ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።