የፓርቲዎች አስተያየት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ

በህወሓት ኃይሎችና የኢትዮጵያ መንግሥት መካከል እየካሄደ ያለውን ጦርንት አስመልክቶ የተለያዩ ፓርትዎችን አስተያየት ሰብስበናል።

መንግሥት በህወሓት ቡድን ላይ የሚወስደውን እርምጃ እንደሚደግፍ የገለጸው ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በንጹሃን ዜጎች ላይ "የሰብዓዊ ጥሰቶች እንዳይፈፀሙ ጥንቃቄ መደረግ አለበት" ሲል አሳስቧል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ በበኩሉ "ጦርነት ለሃገር አያስፈላጊ አይደለም፣ ውይይት መካሄድና ብሄራዊ መግባባት ላይ መድረስ ያሻል" ይላል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲም በመግለጫው "በትግራይ ክልል ያለውን ችግር ህወሓት ከደቀነው አደጋ አንፃር ብቻ በማየት እና ህወሓትን ማሸነፍን ብቻ ዓላማ ያደረገ የአጭር ጊዜ ስልት ይዞ መንቀሳቅስ የለበትም" ነው ያለው።

"በኢትዮዽያ መንግሥትና በህወሓት ኃይሎች መካከል የሚደረገው ጦርነት መፍትሄ አያመጣም" ብሏል። ለዚህም መፍትሄ የሚሆነው የአዳኝና ሽግግር መንግሥት መቋቋም ነው" ያለው ደግሞ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ነው::

የብልፅግና ፓርቲ በበኩሉ "ህወሓት ሃገር ለማፍረስ የተነሳ አሸባሪ ቡድን በመሆኑ ምንም ዓይነት ድርድር አይደረግም። መንግሥት ቡድኑን ለህግ እንዲቀርብ ያደረጋል" ሲል አቋሙን ገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የፓርቲዎች አስተያየት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ